አካል ጉዳተኞችና አቅመ-ደካሞች በድምጻቸው ሐገር የማጽናት ተሳትፏቸውን እያረጋገጡ ነው

You are currently viewing አካል ጉዳተኞችና አቅመ-ደካሞች በድምጻቸው ሐገር የማጽናት ተሳትፏቸውን እያረጋገጡ ነው

AMN – ግንቦት 24/2018 ዓ.ም

የአንድ ድምፅን ታላቅ ዋጋ በመረዳት፣ ያጋጠማቸው ልዩ ልዩ ተግዳሮቶች ሳያስቆማቸው በምርጫው በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ኤኤምኤን ያነጋገራቸው አካል ጉዳተኞችና አቅመ ደካሞች ገለጹ።

በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ወጥተው ድምፃቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ከእነዚህ መራጮች መካከል ወይዘሮ ታገኝ ሙሉጌታ በዕለቱ በህመም ላይ የነበሩ ቢሆንም፣ ሕመማቸውን ወደ ጎን በመተው ይሆነኛልና ያገለግለኛል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ በልደታ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል በሚገኝ አንድ የምርጫ ጣቢያ ተገኝተዋል።

ወይዘሮ ታገኝ የሚሰማቸውን ሕመም ተቋቁመው በምርጫ ጣቢያው እንዲገኙ አቅም የሆናቸውን ሲያስረዱ ለዚህ ያበቃኝ ለሀገሬ ያለኝ ፍቅር ነው ብለዋል።

የአንድ ድምፅን ዋጋ ጠንቅቀው በመረዳትም፣ ጠንካራ የሀገር ፍቅር ስሜታቸውን ሀገርን በሚያጸናው በዚህ ምርጫ ላይ ተሳትፈው አሳይተዋል።

እንደ ወይዘሮ ታገኝ ሁሉ ሌሎች አካል ጉዳተኞችና አቅመ ደካሞችም የቅድመ ምርጫ ካርድ በወሰዱባቸው ጣቢያዎች በመገኘት ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

የምርጫ ጣቢያ አስተባባሪዎች ቅድሚያ በመስጠት አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑን መራጮቹ በደስታ ገልጸዋል፡፡

በታምሩ ደምሴ

See less

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review