ምርጫው በኢትዮጵያ የተገነባውን ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በተግባር የሚያሳይ ነው- ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)

AMN-ግንቦት 24/2018 ዓ.ም

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመላ ሀገሪቱ ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ኦሜጋ ምርጫ ጣቢያ በጠዋቱ ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

የዘንድሮውን ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች በምርጫው ድምፅ ለመስጠት መዘጋቸታቸው ካለፉት ምርጫዎች ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

አሀዛዊ ቁጥሩ እንደሚያመላክተው የመራጩ ቁጥሩ የ2 እና የ3 ሀገራት ህዝብ እንደሆነ ገልፀው፣ ቁጥሩ እንደ ኢትዮጵያ ከ50 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ በኮሮጆና ኮሮጆ ብቻ እንደሚያምን ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።

ይህ የመራጭ ቁጥር የተገነባውን የዲሞክራሲ ስርዓት የሚያሳይ ከሀይል አማራጭ ይልቅ የህዝቦ ድምፅ ዋጋ እንዳለውም ህዝቡ በተግባር ያሳየበት ነውም ብለዋል።

ምርጫችን በካርዳችን ብቻ በመሆኑ የኢትዮጵያን ዲሞክራሲ ለማፅናት ህዝቡ ድምፁ ዋጋ ስላለው የምርጫ ካርዱን እስከ 12 ሰዓት እንዲጠቀምም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሚካኤል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review