AMN-ግንቦት 28/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በየዓመቱ የሚያዘጋጀው የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር የፊታችን ዕሁድ በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን ተገልጿል።
ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ በሚከናወነው ውድድር ከ650 በላይ አትሌቶች እንደሚሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን በተገኘበት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተጠቅሷል። በሴቶች 187 ፣ በወንዶች ደግሞ 466 አትሌቶች ይወዳደራሉ።
ለአትሌቶች የውድድር ዕድል መፍጠር ፣ በስዊድን ለሚካሄደው የግማሽ ማራቶን ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች መምረጥ የውድድሩ ዋነኛ አላማዎች እንደሆኑ ተነስቷል።
መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ባደረገው በዚህ ውድድር ላይ ከ1-6 ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት ይበረከትላቸዋል።
በሁለቱም ፆታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስማቸውን የገነቡ አትሌቶችም እንደሚሳተፉ በፌዴሬሽኑ ፅ/ቤት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተብራርቷል።
ውድድሩ በአዲስ ሚድያ ኔትወርክ በቀጥታ ስርጭት የሚተላለፍ ይሆናል።
በሸዋንግዛው ግርማ