ሸገር ከተማ አስተዳደር ለአርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አስረከበ

You are currently viewing ሸገር ከተማ አስተዳደር ለአርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አስረከበ

AMN – ሰኔ 06/2018 ዓ.ም

በሸገር ከተማ ገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ 1 ሺህ 105 አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል።

በዚሁ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዮ ገልገሎ፤ ቀደም ሲል አርሶ አደሮች ያለበቂ ካሳ ከይዞታቸው ላይ ሲፈናቀሉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

ይህን የተሳሳተ አካሄድ ለመቀየርና አርሶ አደሮችን ማዕከል ያደረገ ልማት ለማረጋገጥ አልሞ ከሦስት ዓመት በፊት ሸገር ከተማ መመሥረቱን ገልጸዋል።

መሬት ሁሉ ነገሩ ለሆነ አርሶ አደር የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማግኘት ትርጉሙ ብዙ እንደሆነም አንስተዋል።

ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ40 ሺህ በላይ የከተማዋ አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ማግኘታቸውን የገለጹት ደግሞ የሸገር ከተማ ካዳስተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዱፌራ ደሜ ናቸው።

በዚህም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የተሰጣቸው አርሶ አደሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መትጋት እንደሚኖርባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቦንጌ ከነ በበኩላቸው፤ ከ5 ሺህ በላይ የክፍለ ከተማው አርሶ አደሮች የይዞታ ማረጋገጫ የተሰጣቸው መሆኑን ገልጸው፤ በዛሬው ዕለት የተካሄደው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ርክክብ መርሃ ግብር በዚህ ዓመት ብቻ ለሦስተኛ ጊዜ የተከናወነ ስለመሆ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review