ጀርመን የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳታፊዋ ኩራሳኦን 7ለ1 አሸነፈች

AMN- ሰኔ 7/2018 ዓ.ም

በ23ኛው የዓለም ዋንጫ በምድብ አምስት ጀርመን የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋን እያደረገች የምትገኘው ኩራሳኦ ላይ ስድስት ግብ አስቆጥራለች።

የአራት ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ ጀርመን 7ለ1 ባሸነፈችበት ጨዋታ ፍሊክስ ንሜቻ ፣ ኒኮ ሽሎቴርበርክ ፣ ካይ ሃቨርትዝ (2) ፣ ጃማል ሙሲያላ ፣ ናትናኤል ብራውን እና ዴኒዝ ኡንዳቭ ግቦቹን አስገኝተዋል።

ኩራሳኦ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ግቧን ሊቫኖ ኮሜኔንሲያ አስቆጥሮላታል።

ትንሿ የካሪቢያን ደሴት በመጀመሪያው 45 የተሻለ ብትፎካከርም በሁለተኛው አጋማሽ ግን የጀርመንን ጫና መቋቋም ተስኗታል።

21ኛ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋን እያደረገች የምትገኘው ጀርመን ምድብ አምስትን መምራት ጀምራለች።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review