የወጣቶች የዲፕሎማሲ ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የአዲስ አበባ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

AMN- ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም

የ6ኛው ዓመታዊ የወጣቶች የዲፕሎማሲ ኮንፈረንስ እና በሞዴል የዲፕሎማሲ ሲሙሌሽን መርሐ ግብር ለመሳተፍ ወደ የአዲስ አበባ የመጡ ተሳታፊዎች በከተማዋ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችንና የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም፤ በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን አድንቀዋል፡፡

እንዲሁም በከተማዋ የተከናወነው የልማት ሥራ ለሌሎች ሀገራት ትልቅ ተሞክሮ እንደሚሆን መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ዓለም አቀፉ ጉባዔ፣ ወጣቶችን ለዲፕሎማሲ፣ ለአመራር፣ ለፖሊሲ ጥናትና ለዓለም አቀፍ ግንኙነት የሚያዘጋጅ የልምድ ልውውጥ መድረክ መሆኑ ተገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review