በኦሮሚያ ክልል ወደ ሰላም የተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎች አጀንዳዎቻቸውን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከቡ

You are currently viewing በኦሮሚያ ክልል ወደ ሰላም የተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎች አጀንዳዎቻቸውን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስረከቡ

በአዲስ አበባ የፈራረሱ ቤቶችን ወደ ዘመናዊ መንደሮች በመለወጥ የዜጎችን ክብርና የከተማዋን ገጽታ መቀየር ተችሏል

AMN – ሰኔ 9/2018 ዓ.ም

ለብዙ ዓመታት በፈራረሱ ፣ ለጤና ጠንቅ በሆኑና መጸዳጃ ቤት በሌላቸው ጠባብ ቤቶች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የአዲስ አበባ ከተማ አረጋውያንና አቅመ-ደካሞች ዛሬ ታሪካቸው ሙሉ በሙሉ ተቀይሯል።

ትናንት በችግር ውስጥ የነበሩት እነዚህ ዜጎች ፣ ዛሬ ሰብዓዊ ክብራቸው በተጠበቀበት አዲስ የኑሮ ዘይቤ ውስጥ መኖር ጀምረዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከባለሀብቶች ፣ ከተለያዩ ተቋማትና ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ጋር በመቀናጀት የጀመረው ይሄው የቤት ግንባታና እድሳት ንቅናቄ መጠለያ ከመስጠት ባለፈ፣ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ማኅበራዊ ፍትሕ ያረጋገጠ ታላቅ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።

የዚህ ንቅናቄ ልዩ ገጽታ ያረጁ ቤቶች ፈርሰው በአዲስ መልክ መገንባታቸው ብቻ አይደለም ፤ ይልቁንም ንጹሕ መጸዳጃ ቤቶችንና ማራኪ አረንጓዴ ስፍራዎችን ያካተቱ ምቹ መንደሮች መፈጠራቸው ጭምር እንጂ።

ተጠቃሚዎች መኖሪያ ቤቶቹን በሚረከቡበት ወቅት ባዶ እጃቸውን አልነበረም ፤ ዘመናዊ የቤት ቁሳቁሶች እንዲሁም ለተወሰኑ ወራት የሚበቃ የምግብ እህል ድጋፍ አብሮ ተበርክቶላቸዋል።

ይህን ግዙፍ በጎ አድራጎት ስኬታማ ለማድረግ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ጉልበታቸውን ፣ እውቀታቸውንና ጊዜያቸውን ተጠቅመው የዜግነት የውዴታ ግዴታቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የሪል ስቴት አልሚዎችና ታዋቂ ባለሀብቶች ሙሉ የመኖሪያ ብሎኮችን በራሳቸው ወጪ በመገንባት ከፍተኛ የዜግነት አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

ይህ ታላቅ ንቅናቄ ዜጎችን ከዝናብ፣ ከብርድ እንዲሁም ካልተመቸ የአኗኗር ዘይቤ መታደግ ብቻ ሳይሆን፣ የንጹሕ መጠጥ ውሃና የመጸዳጃ ቤት ተጠቃሚ በማድረግ ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች የመጋለጥ ዕድላቸውን በከፍተኛ ሁኔታ ቀርፎታል።

ቀደም ሲል የፈራረሱና ለኑሮ ምቹ ያልነበሩ ሰፈሮች ዛሬ በንጹሕና ውብ መንደሮች በመተካታቸው፣ በተለይም ለብቻቸው የሚኖሩ አረጋውያንና ሴቶች አስተማማኝ የደኅንነት ስሜት እንዲሰማቸው ያደረገ ሲሆን፤ በተያያዘም የከተማዋን ገጽታ በአስደማሚ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ሊቀይር ችሏል።

በመንግሥት፣ በሕዝብና በግል ባለሀብቶች የተቀናጀ ትብብር የተገኘው ይህ ስኬት፤ ሕብረተሰባዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ ታላላቅ ማኅበራዊ ችግሮችን እንዴት መቅረፍ እንደሚቻል ትልቅ ማሳያ ሆኗል።

በረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review