AMN-ሰኔ 10/2018 ዓ.ም

እንግሊዝ በ23ኛው የዓለም ዋንጫ ክሮሺያን 4ለ2 በማሸነፍ ጀመረች።
በዳላስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የእንግሊዝን ሁለት ግቦች ሀሪ ኬን በፍፁም ቅጣት ምት እና በጨዋታ አስቆጥሯል።

የባየርን ሙኒኩ አጥቂ በዓለም ዋንጫ ያስቆጠራቸውን ግቦች ከጋሪ ሊንከር እኩል 10 አድርሷል።
ጁድ ቤሊንግሃም እና ተቀይሮ የገባው ማርከስ ራሽፎርድ የእንግሊዝን ቀሪ ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው።
የክሮሺያን ግቦች ማርቲን ባቱሪና እና ፔታር ሙሳ አስቆጥረዋል።
ምድብ 12 ላይ የምትገኘው እንግሊዝ በቀጣይ ጋናን ትገጥማለች። ክሮሺያ ደግሞ ከፓናማ ጋር ትጫወታለች።
በሸዋንግዛው ግርማ