ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ትውልድን የሚያንፁ ትምህርት ቤቶች ድርሻቸው የላቀ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ትውልድን የሚያንፁ ትምህርት ቤቶች ድርሻቸው የላቀ መሆኑ ተገለጸ

AMN- ሰኔ 13/2018 ዓ.ም

ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ትውልድን የሚያንፁ ትምህርት ቤቶች ድርሻቸው የላቀ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ”የትምህርት ቤቶች የግብረ ገብና ፀረ-ሙስና ክበባት የልምድ ልውውጥና ስነ-ምግባር ያሸልማል” በሚል መሪ ሃሳብ የጥያቄና መልስ ውድድር አካሂዷል።

በዚሁ ወቅት የአዲስ አበባ ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጀማል ረዲ፤ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ትውልድን የሚያንጹ ትምህርት ቤቶች ድርሻቸው የላቀ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ምክር ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው፤ ሙስናን ለመከላከል ተከታታይነት ያላቸው ስራዎች ስለመሰራታቸው አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም አሰራሮችን ዲጂታል ማድረግ መጀመሩ ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ የላቀ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል። ይህን መሰል መድረክ ሀገርን የሚያሻግርና ሌብነትን የሚፀየፍ ትውልድ ለመፍጠር ያስችላልም ብለዋል።

በጽዮን ማሞ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review