AMN-ሰኔ 14/2018 ዓ.ም
በ23ኛው የዓለም ዋንጫ ምድብ ስድስት ላይ የምትገኘው ጃፓን ቱኒዚያን 4ለ0 አሸንፋለች።
በጨዋታው አያሴ ኡዳ ሁለት ግብ ሲያስቆጥር ፣ ዲያቺ ካማዳ እና ጁንያ ኢቶ ተጨማሪ ሁለት ግቦችን አስገኝተዋል።
በስዊድን 5ለ1 ከተረታች በኋላ አሰልጣኝ ሳብሪ ላሙቺን ያሰናበተችው ቱኒዚያ ሄርቬ ሬናርድን ብትሾምም የተሻለ ብቃት ማሳየት አልቻለችም።

ጃፓን ከኔዘርላድ እኩል አራት ነጥብ በመያዝ ወደ ጥሎ ማለፍ የመግባት ዕድሏን አስፍታለች። ቱኒዚያ በበኩሏ ከውድድሩ ውጪ ሆናለች።
በቀጣይ የምድብ የመጨረሻ መርሐግብር ጃፓን ከስዊድን ፣ ቱኒዚያ ከኔዘርላንድ ይጫወታሉ።
በምድብ አምስት ኢኳዶርን የገጠመችው የውድድሩ እንግዳ ኩራሳኦ 0ለ0 ተለያይታ የመጀመሪያ ነጥቧን አሳክታለች።
በሸዋንግዛው ግርማ