ለዚህም ከ10 ዓመቱ መሪ እቅድ ጋር የተጣጣሙ ስትራቴጂዎችንና የፖሊሲ ለውጦች ማዕቀፎችን በመንደፍ፤ የመንግሥት፣ የግል ዘርፉንና የህዝብ አጋርነትን በማጠናከር፣ ፈጠራንና የግብርና ቢዝነስን በማስፋፋት እንዲሁም የምግብ ሉዓላዊነትን በማሳደግ የግብርናው ዘርፍ ይበልጥ ምርታማ፣ በገበያ ላይ የተመሰረተ እና ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ቀውሶችን የመቋቋም አቅሙ የዳበረ እንደሆነ ገልጸዋል።
ቀደም ሲል ከውጪ በሚገቡ ምርቶች ላይ በስፋት ተመርኩዛ የነበረችው ኢትዮጵያ አሁን ላይ በሀገር ውስጥ ተተኪ ምርቶችን በማሳደግ፣ የሌማት ትሩፋትና መሰል ሀገር በቀል ተነሳሽነቶችን በማዳበር፣ ቴክኖሎጂንና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በመታገዝ ለወጣቱ የስራ እድልን ከመፍጠር ባሻገር ሀገሪቱ በምግብ ራሷን ለመቻል ለምታደርገው ጉዞ አመርቂ ውጤት እያስገኘ ይገኛል፤ እነዚህ የታቀዱና መጻኢውን ጊዜ ያገናዘቡ ስልታዊ እርምጃዎች ለዘላቂ የግብርና አብዮት፣ ለገጠር ብልጽግና እና ለጠንካራ ኢኮኖሚ መሰረት እየጣሉ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ ወደፊት እየተራመደችና ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበች መሆኑን በተግባር ያሳያሉ።
“ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል የ “ኢትዮጵያ ታከናውናለች” ጉባኤ እተካሄደ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡