ለወራት ያህል በሆርሙዝ ሰርጥ ቆማ የነበረችዉ የኢትዮጵያ መርከብ ወደ ጅቡቲ እያቀናች ነዉ

AMN ሰኔ 17/2018

በቅርቡ በአሜሪካ፣ እስራኤል እና ኢራን መካከል በተነሳው አለመግባባት ሳቢያ ለወራት በሆርሙዝ ሰርጥ ቆመው ከነበሩ መርከቦች መካከል አንዷ የነበረችው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መርከብ MV ጊቤ ዛሬ ከነ ጭነቷ ወደ አጎራባች ወደባችን ወደ ጅቡቲ ወደብ በሰላም እያቀናች ነዉ፡፡

MV ጊቤ የመላው ኢትዮጵያውያን የክብር ምልክት ስትሆን፣ በ347 ዓለም አቀፍ የወደብ መዳረሻዎች የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከሚያውለበልቡ መርከቦቻችን መካከል አንዷ ናት።

MV ጊቤ በአሁኑ ወቅት በኦማን ገልፍ አካባቢ የምትገኝ እና ወደ ጅቡቲ በመጓዝ ላይ ስትሆን፣ እ.አ.አ ሰኔ 28 ከምሽቱ 2:00 አካባቢ ወደ መዳረሻዋ ጅቡቲ ወደብ ትደርሳለች ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ መርከበኞች በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ የነበረውን ከፍተኛ ውጥረትና ዕለታዊ ስጋት በጽናት ተቋቁመዉ ፣ ሀገራዊና ሙያዊ ክብራቸዉን በማስጠበቃቸዉ ምስጋና እየተቸራቸዉ ይገኛል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review