የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብር የነዋሪውን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚመለሱበት እየሆነ ነው

You are currently viewing የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብር የነዋሪውን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚመለሱበት እየሆነ ነው

AMN- ሰኔ 18/2018 ዓ.ም

የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብር የነዋሪውን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የሚመለሱበት እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በ14 መርሐ ግብሮች የታቀፈውን የ2018/19 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ቤቶችን ለማደስ ግንባታ በይፋ አስጀምሯል፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አዲስ አበባ በጎነትን ከበጎ ልጆቿ ያለስስት የተቸረች ሲሆን፣ ያዘመሙና ደሳሳ ጎጆዎቿን አቃንታለች፣ በወጣቶቿም እውቀት ለተማሪዎች አካፍላለች፡፡

በአረንጓዴ አሻራም አዲሱ መልኳን ተኩላለች፤ ይህ ሁሉ በበጎ ፈቃድ ንቅናቄዎች የተከናወነ ነው፡፡

ይህን ስኬት ለማስቀጠልም የዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት መጀመሩ ይታወሳል፡፡

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደርም በ14 መርሐ ግብሮች በርካቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በማሰብ መርሐ ግብሩን የአቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ ግንባታ በማስጀመር በይፋ አብስሯል፡፡

መርሐ ግብሩን ያስጀመሩት የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍጹም ኃይሌ፣ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለነዋሪው የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ፣ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥና ለአዲሱ ትውልድ መልካምነትን የሚያስተምር ነው ብለዋል፡፡

የባለሃብቶችና የተቋማት ተሳትፎ ከዓመት ዓመት እያደገ መምጣቱን ያነሱት ዋና ስራ አስፈጻሚው፣ በዘንድሮው መርሐ ግብር በቤት ልማት ብቻ 1 ባለ 10 ፎቅ አዲስ ህንፃ ግንባታና 280 ደሳሳ ጆጎዎች እንደሚታደሱ ተናግረዋል፡፡

የክፍለ ከተማው የህብረተሰብ ተሳትፎና በጎፈቃድ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዓለሙ ኢመሮ በበኩላቸው፣ የበጎ ፈቃድ ሥራ ዳር ድንበር የለውም በዚህም ዘንድሮ በምናከናውናቸው የበጎ ፈቃድ ስራዎች ክፍለ ከተማውን ከሚዋሰኑ የሸገር ከተሞችን ያሳትፋሉ ብለዋል፡፡

ክፍለከ ተማው በሚያከናውነው የ2018/19 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ700 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የሚሳተፉበት ሲሆን፣ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በታምሩ ደምሴ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review