አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህዝቡን አንገብጋቢ ጉዳዮች በመድረስ ረገድ ውጤታማ ስራ እየሰራ ነው-አቶ በላይ ደጀን

You are currently viewing አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የህዝቡን አንገብጋቢ ጉዳዮች በመድረስ ረገድ ውጤታማ ስራ እየሰራ ነው-አቶ በላይ ደጀን

AMN- ሰኔ 18/2018 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ፈጣን እና መረጃ ሰጪ ከመሆኑ ባሻገር፣ የህዝቡን አንገብጋቢ ጉዳዮች በማንሳት ውጤታማ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ በላይ ደጀን ገለጹ።

ሰብሳቢው ይህንን የገለጹት የከተማዋ ምክር ቤት የፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2018 ዓ.ም የአስፈጻሚ አካላት ማጠቃለያ ሪፖርትን በዛሬው እለት ባዳመጠበት ወቅት ነው።

አቶ በላይ በንግግራቸው፣ ተቋሙ በከተማዋ ተጠያቂነት እንዲሰፍንና ህዝብ ከመንግስት ጋር የበለጠ እንዲቀራረብ ከማድረግ አንጻር ምሳሌ የሚሆን ተግባር እየከወነ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ተቋሙ ያልተቆራረጠ እና ተከታታይነት ያለው፣ እንዲሁም ወቅቱ የሚፈልጋቸውን ትኩስ መረጃዎች እና ፕሮግራሞች ለተደራሲያን በማድረስ ረገድ የበኩሉን እየተወጣ እንደሚገኝ አብራርተዋል። ይህም አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ “የትውልድ ድምጽ” መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ነው ብለዋል።

በአፍወርቅ አለሙ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review