ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በለያቸው ስምንት አጀንዳዎች ላይ የሚደረገው ምክክር ስኬታማ እንዲሆን ምሁራን ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

AMN- ሰኔ 25/2018 ዓ.ም

በቀጣይ በሚካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ወቅት የሚነሱ ጥያቄዎችን እና አለመግባባቶችን ለመፍታት ሙያዊ ድጋፍ ከሚሰጡ ባለሙያዎች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው።

ከሀምሌ 8 ጀምሮ ለአራት ሳምንታት ያህል በሚካሄደው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ወቅት በተወያዮች መካከል መግባባት ባይኖር እና ሙያዊ ድጋፍ የሚሹ ጥያቄዎች ቢፈጠሩ የባለሙያ ድጋፍ ለመስጠት የሚያስችል የባለሙያ ቡድን በኮሚሽኑ ተሰይሟል።

ኮሚሽኑ ከዚህ የባለሙያ ቡድን ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን የባለሙያዎቹ እገዛ አስፈላጊ መሆኑንም ገልጿል።

በሀገራዊው ምክክር ላይ እንዲሳተፉ 4ሺህ ተወካዮች የተለዩ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ደግሞ አንድ ሶስተኛውን እጅ የሚይዙት በሀገሪቱ ከሚገኙ 130 ወረዳዎች የተውጣጡ ተወካዮች ናቸው። የተቀሩት ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት እና የሲቪል ማህበራት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ናቸው፡፡

በአሰግድ ኪዳነማሪያም

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review