ባለፉት የለውጥ ዓመታት ውስጥ 35 ሺህ መዋዕለ ሕፃናት ተገንብተዋል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ባለፉት የለውጥ ዓመታት ውስጥ 35 ሺህ መዋዕለ ሕፃናት ተገንብተዋል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN- ሰኔ 30/2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በትምህርት ዘርፍ የተመዘገቡ ታሪካዊ ስኬቶችንና የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎችን እና የተመዘገቡ ስኬቶች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብራርተዋል፡፡

በትምህርት መሠረተ ልማት ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ትስስር እና በሰው ኃይል ልማት ላይ የተጀመሩት ሥራዎች የሀገሪቱን የነገ ዕጣ ፈንታ ለመወሰን ታስበው፣ በረጅም ጊዜ ኢንቨስትመንት መርህ እየተከናወኑ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ብቻ 35 ሺህ የሚሆኑ መዋዕለ ሕፃናት መገንባታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል፡፡

ይህ የኢንቨስትመንት ቁጥር በቀላሉ ሊደረስበት የማይችል ታሪካዊ ስኬት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ሕፃናት ዛሬ ላይ ምርጫ እንደማይመርጡ እናውቃለን ነገር ግን ከ20 ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ ምን እንደሚሆን ስለምናውቅ፣ ትኩረታችን ከአጭር ጊዜ የፖለቲካ ትርፍ ይልቅ በረጅም ጊዜ ትውልድ የመቅረጽ ኢንቨስትመንት ላይ ነው ብለዋል፡፡

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review