ሀገራዊ ምክክሩ የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላምና ታላቅነት ለመገንባት የተገኘ ታሪካዊ ዕድል ነው

AMN- ሐምሌ 7/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የገጠሟትን ዘመናዊና ሥር የሰደዱ ችግሮች በውይይት ለመፍታትና ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ የተገኘውን ሀገራዊ የምክክር ዕድል በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ምሁራን አስገነዘቡ።

የፖለቲካል ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ ዳምጠው ተሰማ (ረ/ፕ) እንዳሉት፤ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በውይይት የውስጥ ጉዳዮችን ለመፍታት የነበሩ ዕድሎች በተለያዩ ምክንያቶች መክነው አልፈዋል፡፡

የአሁኑ ትውልድ ካለፈው ታሪክ በመማር አሁን ያለውን የምክክር ሂደት በአግባቡ ሊጠቀምበት እንደሚገባም መክረዋል።

ምክክር የሚደረግባቸው ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎችም የእያንዳንዱን ዜጋ የወደፊት ዕጣ ፋንታ የሚወስኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የሕግ ምሁሩ ዓለማየሁ ገብረማርያም (ፕ/ር) በበኩላቸው፤ ይህንን የምክክር ሂደት በአግባቡ ከተጠቀምንበት የሀገርን ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥና የበለጸገች ኢትዮጵያን ማንበር ይቻላል ብለዋል፡፡

ምሁራኑ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ ፖለቲካዊ ትግልን በትጥቅ ለመፍታት መሞከር ዘላቂ መፍትሔ እንደማያመጣ አስገንዝበው፤ በዓለም ታሪክ የታዩ ታላላቅ ጦርነቶችና ማኅበራዊ ቀውሶች ሁሉ በመጨረሻ በጠረጴዛ ዙሪያና በድርድር መቋጨታቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review