የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች ያስተላለፉት መልዕክት

AMN ሀምሌ 7/2018 ዓ.ም

ክቡራትና ክቡራን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳታፊዎች

ታሪካዊ በሆነው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሳትፎ ለማድረግ የመጣችሁትን ወገኖቼን ለመቀበል በመታደሌ ታላቅ ክብር ይሰማኛል። እናንተ በዚህ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ስትመጡ የወከላችሁትን ማህበረሰብ ድምፅና ምኞት ለማስተጋባት ብቻ ሳይሆን ለሀገራችን የጋራ ዕድልና የወደፊት ዕጣ ፈንታ መሠረት ለመጣል ጭምር በመሆኑ ትከሻችሁ ላይ የወደቀው ኃላፊነት እጅግ ታላቅና ጥልቅ ነው። በምክክራችሁ የምትደርሱባቸው ውሳኔዎች፣ የምትፈጥሩት መግባባት እንዲሁም የምታጸኑት ስምምነት ከዚህ የታሪክ ወቅት ባለፈ ዘልቆ የሚቀጥልና ለሰላማዊት፣ ለዴሞክራሲያዊትና ለተግባባች ኢትዮጵያ መሠረት የሚጥል ነው። ምክክራችሁ በጥበብ፣ በጋራ መከባበርና ለሕዝብ ጥቅም ባላችሁ ጽኑ ቁርጠኝነት እንዲመራ እንዲሁም ለመጪው ትውልድ ብሩህ ነገን የሚያሰናዳ እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።

ፕሮፌሰር መሥፍን አርአያ

ዋና ኮሚሽነር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review