ኢትዮጵያ እና ሞሪሺየስ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ ገለጹ

AMN ሐምሌ 7/2018

ኢትዮጵያ እና ሞሪሸስ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በጋራ እንደሚሰሩ አስታወቁ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ ከሞሪሸስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቪንቻንድራ ራምጉላም ጋር በመገናኘት፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከ መልዕክት አድርሰዋል።

አምባሳደር ሃደራ ከጠቅላይ ሚኒስትር ናቪንቻንድራ ራምጉላም ጋር ባደረጉት ውይይት፣ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።

ኢትዮጵያ ከሞሪሸስ ጋር ያላትን የቆየ ግንኙነት ለማጠናከርና በጋራ ፍላጎቶች ላይ በትብብር ለመስራት ትልቅ ትኩረት እንደምትሰጥም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ራምጉላም በበኩላቸው ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን አስደናቂ እድገትና ለዚህ ስኬት አስተዋፅኦ ያበረከተውን አመራር አድንቀዋል።

ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያና በሞሪሸስ መካከል ያለውን ግንኙነት በተለያዩ ዘርፎች ለጋራ ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያላቸውን ጠንካራ ቁርጠኝነት መግለጻቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review