AMN ሐምሌ 7/2018

ነገ የሚጀመረው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ለሀገራዊ መግባባት መሰረት የሚጣልበት ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አሕመድ ሁሴን ገለጹ።
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አሕመድ ሁሴን ነገ የሚጀመረውን ሀገራዊ የምክክር መድረክ አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ይህ ምክክር በሀገሪቱ ታሪክ የቆዩና ስር የሰደዱ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ትልቅ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህ ታሪካዊ መድረክ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ በጥልቀት በመዳሰስ፣ ለጋራ መግባባትና ለዘላቂ ሰላም መንገድ የሚጠርግ ነው ብለዋል።
ለምክክሩ ውጤታማነት ሁሉም ኢትዮጵያዊ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለበትም ጥሪ አቅርበው ለሂደቱ ስኬታማነትም ምክር ቤቱ የተለመደውን የትብብር ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸዉን ኢዜአ ዘግቧል፡፡