ስፔን ፈረንሳይን በማሸነፍ ለፍፃሜ አለፈች

You are currently viewing ስፔን ፈረንሳይን በማሸነፍ ለፍፃሜ አለፈች

AMN-ሐምሌ 7/2018 ዓ.ም

ስፔን የውድድሩ ምርጥ ቡድን የተባለችው ፈረንሳይን 2ለ0 በማሸነፍ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰች።

በዳላስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሚኬል ኦያርዛባል በፍፁም ቅጣት ምት ፣ ፔድሮ ፖሮ በጨዋታ ያስቆጠሯቸው ግቦች ስፔንን ባለ ድል አድርገዋል።

ጨዋታውን የማሸነፍ ሰፊ ግምት ተሰጥቷት የነበረችው ፈረንሳይ ደካማ ብቃት አሳይታ ከውድድሩ ተሰናብታለች። በተለይ ብዙ የተነገረለት የማጥቃት ጥንካሬዋ በስፔን የተደራጀ መከላከል ከጥቅም ውጪ ሆኗል።

ስፔን በአንፃሩ በዘንድሮ ውድድር ምርጡን ብቃት በማሳየት የፍፃሜ ተፋላሚ መሆኗን አረጋግጣለች።

በሊውስ ዴ ላ ፉኤንቴ የምትመራው ስፔን ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ስትበቃ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። ከዚህ ቀደም በ2010ሩ የደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫ ለፍፃሜ ደርሳ ኔዘርላንድስን በማሸነፍ ዋንጫ ማንሳቷ ይታወሳል።

ስፔን በፍፃሜው የአርጀንቲና እና እንግሊዝ አሸናፊን ትፋለማለች።

ስፔን በፍጻሜዉ ጨዋታ ከማን ጋር ትገናኝ ይሆን ? ግምትዎን ያጋሩን!

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review