AMN-ሐምሌ 8/2018 ዓ.ም
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና መላው ኢትዮጵያውያንን ለምክክር ያሰባሰበው ታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ በአዲስ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄድ ጀምሯል፡፡
ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ማካሄድ የጀመረችው ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ፤ ለአሁኑም ሆነ ለቀጣዩ ትውልድ የምሥራች ነው።

ጉባዔው በሕዝቧ መግባባት እና በጋራ ትርክት ላይ የምትገነባ መሆኗንም የሚያረጋግጥ ወሳኝ የሀገር ግንባታ ሂደት ጭምር ነው።
በምክክር ጉባኤው ከመላው ኢትዮጵያ የተወጣጡ 4 ሺህ ተመካካሪዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡