ሕዝባዊ አንድነትና አካታች አስተዳደር የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል ወሳኝ ናቸው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ሕዝባዊ አንድነትና አካታች አስተዳደር የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል ወሳኝ ናቸው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም

‎በመደመር እሳቤ እየተመራን፤ ሕዝባዊ አንድነትን፣ ተጠያቂነትንና አካታች አስተዳደርን ማረጋገጥ የፖለቲካ አመራር የዜጎችን ሕይወት እንዲያሻሽል የሚያስችሉ ወሳኝ መሠረቶች ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) “ለዕድገት መምራት” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ መካሔድ በጀመረው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገዋል።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተለለፉት መልዕክት፣ የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ ይህንን ታላቅ አህጉራዊ መድረክ ማስተናገዷ ለሁላችንም ታላቅ ኩራት ነው ብለዋል።

በመደመር እሳቤ እየተመራን፤ ሕዝባዊ አንድነትን፣ ተጠያቂነትንና አካታች አስተዳደርን ማረጋገጥ የፖለቲካ አመራር የዜጎችን ሕይወት እንዲያሻሽል የሚያስችሉ ወሳኝ መሠረቶች ናቸው ብለዋል።

‌‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ይህም ፓርቲዎች ከምርጫ ውድድር ባለፈ አሻግረው እንዲመለከቱ፣ በመንግሥት ለውጦች የማይቀያየሩ፣ ብሔራዊና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ እና ለሀገር ጥቅም በጋራ እንዲሠሩ ይጠይቃል ነው ያሉት።

በሌላ በኩል፣ ተተኪው ትውልድ ኃላፊነቶችን እየወሰደ የሚያድግበትን ዕድሎችን እያገኘ እንዲሄድ ለማድረግ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑንም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ በኩል የምትሰጠውን ሥልጠና በአህጉሪቱ ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፍት ማድረጓን ትቀጥላለች ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎አክለውም ለሕዝባችን የተሻለ መጻኢ ዕድል የመገንባት ኃላፊነታችን ሊቀጥል ይገባል በማለት አስገንዝበዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review