AMN- ጥቅምት 27/2019 ዓ.ም
አዲስ አበባ የአፍሪካ የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዲናነቷን በተግባር እያረጋገጠች ነው፡፡
የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል አዲስ አበባ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱ ትልልቅ የቱሪዝም ኮንፈረንሶችንና ጉባኤዎችን ለማስተናገድ ያላትን አቅም በከፍተኛ ደረጃ እያጠናከረች ትገኛለች።
ከተማዋ ያሏትን ተፈጥሯዊ ጸጋዎች ከዘመናዊ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎች ጋር በማጣመር አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁነቶችን በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ያላትን ዝግጁነት በተግባር እያረጋገጠች ነው።
በቅርብ ዓመታት የተከናወኑት የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች፣ አዳዲስ የመዝናኛና የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች ግንባታ ጥራት ማደግ ከተማዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ አድርጓታል።
ይህ ስኬት አዲስ አበባ በአፍሪካ የቱሪዝም ኮንፈረንስ ተመራጭነቷን የበለጠ የሚያጠናክር ከመሆኑም በላይ ለሀገሪቱ የቱሪዝም ገቢና ለኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።
ትልልቅ ጉባኤዎች በአዲስ አበባ መካሄዳቸው ለከተማዋ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን ከማጎልበት ባሻገር አህጉራዊ መድረኮች የአዲስ አበባንና የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ትልቅ እድል ይፈጥራሉ።

አዲስ አበባ የኮንፈረንስ ቱሪዝም አቅሟን ማጠናከሯ በቀጣይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልልቅ ስብሰባዎችንና ኤክስፖዎችን በመሳብ በአፍሪካ ቀዳሚዋ የጉባኤዎችና የቱሪዝም ማዕከል ሆና እንድትቀጥል ያስችላታል።
የኮንፈረንስ ቱሪዝም ተመራጭነቷን ያጠናከረችው አዲስ አበባ ከዛሬ ጀምሮ 2ኛውን የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባዔን ማስተናገድ ጀምራለች። የአድዋ ድል መታሰቢያ በአፍሪካዊ ቀለም ደምቆ እንግዶችን እያስተናገደ ይገኛል።
አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌቷ ኢትዮጵያ ያለፉት የለውጥ ዓመታት የልማት ጉዞ ስኬቶቿን በጉባኤው ታጋራለች ተብሎ ይጠበቃል።
በየሻምበል ምህረት