የህክምና ተራ እየጠበቁ ያሉ የልብ ህሙማን ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ ከኸርት አታክ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን ጋር ተቀናጅተን ለመስራት ተስማምተናል – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ለ5ኛ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከ700 በላይ የልብ ህሙማንን በማከም

ከስቃይ ያዳኑት Heart Attack Ethiopia (የኸርት አታክ ኢትዮጵያ) ፋውንዴሽን መስራቾችን እና የበጎ ፍቃድ ቡድኑን በጽ/ቤታችን ተቀብለናቸዋል ብለዋል፡፡

የኸርት አታክ ኢትዮጵያ ፋውንዴሽን እና የበጎ ፍቃድ ቡድኑ በፍቅር የምትሰጡት እጅግ የላቀ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ከልብ የሚደነቅ ነው ።

በቀጣይም የህክምና ተራ እየጠበቁ ላሉ የልብ ህሙማን ፈጣን ምላሽ እንዲያገኙ በጋራ ተቀናጅተን የብዙዎችን ሕይወት ለመታደግ አብረን ለመስራት ተስማምተናል ብለዋል፡፡

እንደዚህ ትልቅ የህክምና ቡድን አቀናጅታችሁ ለወገኖቻችሁ ትልቅ ህይወትን የማዳን ስራ ለመተግበር የተጋችሁ መስራቾቹን እና የበጎ ፍቃድ የህክምና ቡድኑን አባላት በራሴ እና በታካሚዎች ስም ከልብ አመሰግናለሁ ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review