ኢትዮጵያ ያላትን የኃይል ሀብት በአግባቡ የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን አስጠብቃ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን ትገነባለች – የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

You are currently viewing ኢትዮጵያ ያላትን የኃይል ሀብት በአግባቡ የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን አስጠብቃ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን ትገነባለች – የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

AMN – ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ ያላትን የኃይል ሀብት በአግባቡ የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን አስጠብቃ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ አስታወቁ።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ የታላቁ የህዳሴ ግድብ በራስ አቅም መገንባቱ የሀገሪቱን ጽናትና ጀምሮ የመጨረስ አቅም በተግባር ያረጋገጠ ታላቅ ምዕራፍ መሆኑን ገልፀዋል።

የግድቡ መጠናቀቅ እና የውሃ ሙሌት ሂደት የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጭምር ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ፣ ቀደም ሲል ይነሱ የነበሩ መሠረተ ቢስ ስጋቶች ፍጹም ሐሰተኛ መሆናቸውን ማሳያ ነው ብለዋል።

ሀገሪቱ ታላቁ የህዳሴ ግድብን ከማጠናቀቅ ባሻገር፣ የቀድሞ ጥናቶችን በመከለስ እና አስፈላጊውን ፋይናንስ በማሟላት ተጨማሪ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ገልፀዋል።

አሁንም ወደፊትም ትልቁ የኃይል ምንጭ በአባይ ወንዝ ላይ የሚኖር ነው ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ማንም አካል ኢትዮጵያን ከዚህ የልማት ጉዞዋ ሊያስቆማት እንደማይችል አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ ከምታመነጨው ንጹህ የኤሌክትሪክ ኃይል ጎረቤቶቿ እንዲቋደሱ በማድረግ የመደመር እሳቤን በተግባር አሳይታለች።

የሳይንስ መሠረት የሌላቸው ተቃውሞዎች እና የቀድሞ ያልተገባ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚደረጉ ሙከራዎች የሀገሪቱን የልማት ግስጋሴ ሊያስተጓጉሉ እንደማይችሉ ዋና ሥራ አስፈፃሚው አጽእኖት ሰጥተዋል ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አክብራ፣ የሀብት ትሩፋቷን ለአፍሪካውያን እያካፈለች የኢኮኖሚ ትንሳኤዋን ያለማቋረጥ ታስቀጥላለች።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review