አዲስ እንዴት ዋለች?- ከኤ ኤም ኤን ዲጂታል ሚዲያ

AMN- ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም

👉 ከመላ አመራሮች ጋር በክረምት ወቅት የሚሰሩ የክረምት በጎ ፍቃድ ስራዎች፣ የቤት ግንባታ፣ የጎርፍ አደጋን መከላከል፣ የፅዳት ስራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ፣ ማዕድ ማጋራት፣ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት፣ ደም ልገሳ ፣ተረጅነትና ድህነት ቅነሳ ስራዎች አፈፃፀም መገምገማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በሁሉም መስክ ውጤታማ ተግባራት እየተፈፀሙ መሆኑን አረጋግጠናል ያሉ ሲሆን ሆኖም በክፍለ ከተሞች እና በተቋማት መካከል የአፈፃፀም ልዩነቶች ይታያሉ ብለዋል።

👉 የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ የቤተ መንግሥት አስተደደር እና የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራር እና ሰራተኞች በቆቃ ቤተ መንግሥት አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሀይ ጳውሎስ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ አረንጓዴ ዐሻራ የተጎዱ በርካታ አካባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።

👉 በ49ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ለመሳተፍ የአፍሪካ ሀገራት ልዑካን ቡድን አዲስ አበባ እየገቡ ነው።

በዚሁ መሠረት የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ዶክተር ኤድዋርድ ቢዚማና፣ የዚምባብዌ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፕሮፌሰር አሞን ሙርቪራ፣ የናይጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ቢአንካ ኦዶሜጉ-ኦጁክው እንዲሁም የናሚቢያ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ንግድ ሚኒስትር ሰልማ አሺፓላ-ሙሳቪ አዲስ አበባ ገብተዋል።

👉 የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በአፍሪካ የአሜሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) አዛዥ ጀነራል ዳግቪን አንደርሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የመከላከያ ትብብር፣ በቀጣናዊ ደህንነት እና በጋራ የሚከናወኑ የወደፊት የትብብር መስኮች ላይ መክረዋል።

👉 ኢትዮጵያ ከአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) ጋር በመተባበር የምታስተናግደው የአፍሪካ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚዬም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በመርሀ ግብሩ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አንደርሰን፣ የመከላከያ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል፣ የሀገራቱ የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች እና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የጦር መሪዎች ታድመዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review