የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከናሚቢያ እና ቦትስዋና አቻዎቻቸው ጋር ተወያዩ

You are currently viewing የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከናሚቢያ እና ቦትስዋና አቻዎቻቸው ጋር ተወያዩ

AMN- ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ እየተካሄደ ካለው 49ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጎን ለጎን ከናሚቢያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሴልማ አሺፓላ-ሙሳቪይ እና ከቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ‎ዶክተር ፌንዮ ቡታሌ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ሚኒስትሩ ከናሚቢያ አቻቸው ጋር ባደረጉት ውይይት የሁለቱን አገራት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በተለይም በአየር ትራንስፖርት እና በቆዳ ኢንደስትሪ ዘርፎች ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው አግባቦች ተወያይተዋል።

በተመሳሳይ ሚኒስትሩ ከቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ‎ዶክተር ፌንዮ ቡታሌ ጋር ባደረጉት ውይይት ቦትስዋና ከኢትዮጵያ አረንጓዴ ልማት፣ መሠረተ ልማት ግንባታ እና በከተሞች የኮሪደር ልማት ልምድ የመቅሰም ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሚኒስትሮቹ ጋር ባደረጉት ውይይት ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ በአሕጉራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን በፓን አፍሪካኒዝም መርህ የአፍሪካውያን ቤት የሆነውን አፍሪካ ሕብረት በሚጠናከርበት እና ውጤታማ ሥራ በሚሰራበት መንገድ ላይ መወያየታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review