ከለውጡ ወዲህ በመሠረተ ልማት ግንባታ አመርቂ ውጤት ተገኝቷል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

You are currently viewing ከለውጡ ወዲህ በመሠረተ ልማት ግንባታ አመርቂ ውጤት ተገኝቷል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN – ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም

በአማራ ክልል ባለፉት ጥቂት ዓመታት የጸጥታ ችግሮችና የተለያዩ መስተጓጎሎች ያጋጠሙ ቢሆንም፣ በመሠረተ ልማት ግንባታ አመርቂ ውጤት መገኘቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ በክልሉ ያጋጠሙ ውስብስብ ተግዳሮቶችን በመሻገር በተለያዩ የልማት ዘርፎች ዘመናትን የሚሻገሩ ስኬቶች መመዝገባቸውን አብራርተዋል።

በመሠረተ ልማት ግንባታ ረገድ በተለይም የመንገድ ዘርፉን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የክልሉ የመንገድ ሽፋን ከነበረበት በእጥፍ በማደግ 4 ሺሕ 500 ኪሎ ሜትር መድረሱን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅትም 61 ተጨማሪ የመንገድ ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ ለከተማዋ ውበትና ማራኪ ገጽታ ትልቅ ድርሻ ያለው ዘመናዊው የባሕር ዳር ድልድይም ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል።

በክልሉ ትልቅ ትኩረት ተሰጥቶ ከተከናወኑ ሥራዎች መካከል የደብረ ማርቆስ አየር መንገድን ጨምሮ፣ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ቀጥሎ ትልቁ የሆነው የባሕር ዳር አየር መንገድ ተርሚናል እንዲሁም የኮምቦልቻ ተርሚናል ተገንብተው ለአገልግሎት መብቃታቸውን ተናግረዋል።

የተወሳሰቡ ሁኔታዎችን አልፎ የቀጠለው የአዋሽ-ኮምቦልቻ- ሐራ ገበያ የባቡር ሐዲድ ዝርጋታ ፕሮጀክት በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም ጠቅሰዋል።

በመሠረተ ልማት፣ በቱሪዝም እና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ከለውጡ ወዲህ የተሠሩት ሥራዎች፣ ባለፉት 20 እና 30 ዓመታት ከተከናወኑት የሚበልጡ እንጂ የሚያንሱ እንዳልሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።

በበረከት ጌታቸው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review