AMN- ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሀሳብ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ከማለዳው 12:00 ሰዓት ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ የመርሐ ግብሩን የእስከ አሁን ሂደት በተመለከተ ከሁኔታ መከታተያ እና የመረጃ ማደራጃ (Situation Room) ማዕከል መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም እስከ ጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ 200 ሚሊዮን ችግኞች መተከላቸውንም ሚኒስትሯ አብራርተዋል።
በመርሐ ግብሩ 5.9 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን አሻራቸውን እያሳረፉ ነው ብለዋል።