አረንጓዴ ዐሻራችን እንደ ትውልድ ያሳካነው እና የመተባበርን ውጤት አድምቀን የጻፍንበት ብሔራዊ ድላችን ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN- ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም

አረንጓዴ ዐሻራችን እንደ ትውልድ ያሳካነው እና የመተባበርን ውጤት አድምቀን የጻፍንበት ብሔራዊ ድላችን ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ከጀግናው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ጋር ዐሻራችንን አሳርፈናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ልጆች በሕብረት ከወጡ፣ ክንዳቸውን ለትብብር ከዘረጉ ሁሌም ድል አለ ሲሉ የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሁሌም ማሸነፍ፣ ሁሌም መፈጸም መኖሩን ዛሬም አሳይተዋል ነው ያሉት።

ባለፉት ጊዜያት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሮች ታሪክ ሰርተናል ያሉ ሲሆን ዛሬም እንደ ሕዝብ በምንም ሳንለያይ ባደረግነው ከፍተኛ ርብርብ ውጤት አስመዝግበናል ብለዋል።

የዘንደሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር እንደዚህ ቀደሞቹ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነቱን እና ጥንካሬውን በተግባር ያረጋገጠበት ታሪካዊ ውሎ እንደነበርም ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review