የለውጥ ጉዞው የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽ አድርጓል

AMN- ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም

የለውጥ ጉዞው የነዋሪዎችን የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽና ፈጣን ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አዋሌ መሐመድ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ በተቋሙ ላለፉት ሦስት ዓመታት በተሠሩ 46 ጥናትና ምርምሮች የተደገፉ የቴክኖሎጂ አማራጮች በከተማዋ ተግባራዊ እየተደረጉ ነው፡፡

የሳይበር ደኅንነትን ማስጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ ለዚህም ተቋሙ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን እያለማ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ተቋማት ተደራሽ እያደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከልም ከ150 በላይ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ነዋሪዎች አገልሎት እያገኙ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በአዲስ መሶብ የተንቀሳቃሽ አውቶቡስ አገልግሎትም 48 ዋና ዋና አገልግሎቶች ተደራሽ መደረጉን አመላክተዋል፡፡

አዲስ አበባን ከጊዜው ጋር የሚመጥን፣ ዘመናዊና የተቀላጠፈ የአኗኗር ዘይቤ ወዳላት ስማርት ሲቲ ከተማነት ለመቀየር እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

የለውጥ ጉዞው የነዋሪዎችን የዕለት ተዕለት ኑሮ ያቃለለ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽና ፈጣን ያደረገ እንዲሁም አዲስ አበባን በአፍሪካ ደረጃ ተወዳዳሪና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ መናኸሪያ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

የሻምበል ምህረት

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review