ለመስቀል ደመራ እና ለእሬቻ በዓላት ወደ መዲናዋ የሚመጡ እንግዶችን በፍቅር ለማስተናገድ ተዘጋጅተናል – በጎ ፈቃደኞች

You are currently viewing ለመስቀል ደመራ እና ለእሬቻ በዓላት ወደ መዲናዋ የሚመጡ እንግዶችን በፍቅር ለማስተናገድ ተዘጋጅተናል – በጎ ፈቃደኞች

AMN – መስከረም 13/2019 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ እንግዶቿን ተቀብላ የምታስተናግ ምቹ ከተማ መሆንዋን ለማሳየት ለመስቀል ደመራ እና ለእሬቻ በዓላት ወደ መዲናዋ የሚመጡ እንግዶችን በፍቅር ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን የአዲስ አበበ ከተማ በጎ ፈቃደኞች ገልጸዋል፡፡

የመስቀል ደመራና የእሬቻ በዓላት አከባባር ላይ የበጎ ፈቃደኞች ስምሪት የተሰጠበት የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሚኤሳ ኢሌማ መስከረም ኢትዮጵያ በሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት ብቻ ሳይሆን በተፈጥሮ አጊጣ የምትደምቅበት በመሆኑ በርካታ የውጭ ሀገር ጎብኚዎች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማን ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ፍሬ የሚያፈሩበት ወር በመሆኑ በልዩ ትኩረት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡

የውይይቱ ተሳተፊ በጎ ፈቃደኞች አዲስ አበባ ከተማን ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ለማድረግ የተሰሩ የኮሪደር ልማቶችና ታላላቅ ፕሮጀክቶች ያስገኙትን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ለማጠናከርና ቱሪስቶች የሚመርጧት መዳረሻ ለማድረግ የዓደባባይ በዓላት ሚና የላቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በጎ ፈቃደኖቹ በዓላቱን ኢትዮጵያ የምትደምቅበት ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም መናገራቸውን የአበባ ከተማ አስተዳዳር የሰላምና ጸጥታ አስተዳዳር ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በጎ ፈቃደኞች እንግዶችን ተቀብለው በማስተናገድ ለሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት መጠናከርና በብዝሀንት ላይ የተመሰረተ ኢትዮጵያዊ ማንነት እንዲጎለበት ለማድረግ ያሳዩት ተነሳሽነት ለአዲስ አበባ ከተማ እድገትና ብልጽግና የለቀ ፋይዳ እንዳለው ዶክተር ሚኤሳ አገልዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ኅብረተስ ተሳፎና በጎ ፈቀድ ማስተባባሪያ ኮመኒሽን ምክትል ኮሚሽነር ወይዘሮ አስራት ንጉሴ በበኩላቸው በጎ ፈቃደኞች በዓላቱን ለማክበር ወደ አዲስ የሚገቡ እንግዶችን በፍቅር ተቀብልው ማስተናገድ የሚያስችል ግንዛቤ እንደተፈጠረላቸው የገለጹ ሲሆን በዓላቱን ወግና ስርዓቱን በጠበቀ መንገድ ለማክበር የሚያያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

በዓላቱ በሰላም እንዲከበሩ ከተማ አስተዳዳሩ ዝግጁ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የሰላምና ጸጥታ አስተዳዳር ቢሮ አማካሪ አቶ ጌታሁን አበራ በጎ ፈቃደኞች በዓላቱ ትውፊታቸውንና ወጋቸውን ጠብቀው ማክበር የሚያስችል ግንዛቤ መፍጠራቸው ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review