ከ500 በላይ አምራቾች የሚሳተፉበት ኤክስፓ ከመጭው ነሃሴ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሊካሄድ ነው

AMN – ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም

የ2019 አዲስ አመት ዋዜማ ኤግዚብሽን፣ ባዛርና ኤክስፓ አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ በቀን 15ሺ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ የሚጠበቀው ይኸው መርሃ ግብር እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ በሚኖረው ለ21 ቀናት ቆይታ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ሰዎች ይመለከቱታል ተብሏል።

ከሀገር ውስጥ አምራቾችና ነጋዴዎች ባለፈ የቱርክ:የህንድና የሳውድ አረብያ ነጋዴዎች የሚሳተፉ ይሆናል።

መርሃ ግብሩ ኢትዮ ቴሌኮምና ዳሽን ባንክ ከሴንቸሪ ፕሮሞሽን ጋር በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን አምራቾች ምርትና አገልግሎታቸውን ከማስተዋወቅ ባለፍ ሸማቾች የሚፈልጓቸውን ምርቶች በአቅራብያቸው ለማግኘት እድል ይፈጥራል ተብሏል።

በኤግዚብሽን:ባዛርና ኤክስፓ ማጠቃለያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካን ጨምሮ የተለያዩ የሽልማት መርሃ ግብሮች ሰለመዘጋጀቱን ነው የተመላከተው።

በመሀመድ ቶፊቅ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review