ኤርሊንግ ሀላንድ በድንቅ የእግር ኳስ የጨዋታ ዘመን ስኬቶቹ ከጊነስ የዓለም ክብረወሰን የምስክር ወረቀቶች ተበርከቱለት

AMN- ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም

አዲሱ የውድድር ዘመን ሊጀምር ጥቂት ቀናት በቀሩበት በዚህ ወቅት፣ የበርካታ ክብረ ወሰኖች ባለቤቱ ኤርሊንግ ሀላንድ እስከ አሁን ባሳየው ድንቅ የእግር ኳስ የጨዋታ ዘመን ስኬቶቹ ከጊነስ የዓለም ክብረወሰን የምስክር ወረቀቶች ተበርክተውለታል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ፣ በአውሮፓ ኔሽንስ ሊግ 19 ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች በመሆን እና በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ባደረጋቸው 111 ጨዋታዎች በፈጣን ጊዜ 100 ግቦችን ያስቆጠረ በሚል ዕውቅና ተሰጥቶታል፡፡

እንዲሁም በአንድ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን 36 ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ ከፍተኛ ግብ በማስቆጠር እና በአንድ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ 5 ግቦችን በማስቆጠር ከፍተኛ ግብ ያስቆጠረ በሚል ከሊዮኔል ሜሲ እና ሉዊዝ አድሪያኖ ጋር ማዕረግ ተጋርቷል፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review