AMN- ነሐሴ 7/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ ደንብ ማስከበር ምክትል ስራአስኪያጅ እና የቀድሞ የልደታ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በነበሩት ወ/ሮ አበባ እሸቴ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ምክትል ስራአስኪያጅ እና የቀድሞ የልደታ ክፍለከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በነበሩት ወ/ሮ አበባ እሸቴ ህልፈት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።
ለመላው ቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና የስራ ባልደረቦቻቸውም መፅናናትን ተመኝተዋል።
ፈጣሪ ነብሳቸውን በአፀደ ገነት ያኖር ዘንድም ተመኝተዋል፡፡