“አዲስ የኬክ ኤክስፖ” የፊታችን ሐሙስ ጀምሮ በአራዳ ፓርክ ይካሄዳል

AMN- ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም

“አዲስ የኬክ ኤክስፖ” ከነሐሴ 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ አራዳ ፓርክ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኬክ፣ የዳቦ እና ጣፋጭ ምርቶች ዘርፍን ለማስተዋወቅ ያለመው አዲስ የኬክ ኤክስፖ ለ3ኛ ጊዜ ነው የሚካሄደው፡፡

የአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ከአዲስ ከስተም ሆልዲንግ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ኤክስፖ የኬክና የጣፋጭ ምርቶች ዘርፍን ለማስተዋወቅ፣ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችንና ተቋማትን ለማገናኘት እንዲሁም የከተማዋን የቱሪዝም ንግድና የኤግዚቢሽን አቅም ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው ኤክስፖ ከሀገር ውስጥ እና ከውጪ የሚመጡ የኬክና የጣፋጭ ምርት አምራቾች፣ ባለሙያዎችና የዘርፉ ተዋናዮች ምርቶቻቸውንና የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ለጎብኚዎች እንደሚያቀርቡ የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ዝግጅቱ የንግድ ትስስርን ከመፍጠር ባለፈ የከተማዋን የቱሪዝም፣ የንግድና የኤግዚቢሽን አቅም ለማስተዋወቅ እንደሚያግዝም ተመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review