AMN- ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ በቂ የመዝናኛ ቦታዎችን ለማቅረብ ከለሙ ቦታዎች አንዱ የሆነው አራዳ ፓርክ ለከተማዋ ነዋሪዎች ምቾት ብሎም ለቱሪስት ፍሰት ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ አራዳ ፓርክ ለወጣቶች፣ ለአዛውንቶች፣ ለህፃናት፣ ለስፖርተኞች፣ ለነጋዴው እንዲሁም ለተማሪዎች በጠቅላላ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች በነፃ የቀረበ የጋራ መገልገያ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በከተማችን የገነባነው ውቡ የአራዳ ፓርክ ለሁሉም ማህበረሰቦች በእኩልነትና አካታች በሆነ መንገድ በነፃ የቀረበ የጋራ መገልገያ ስፍራ ነው፡፡ ፓርኩ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠርም በላይ ቱሪዝምን በማሳደግ ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታልም ነው ያሉት፡፡