ጽዳትና ውበት ዓለም ዓቀፍ ተወዳዳሪነት – አዲስ አበባ!

You are currently viewing ጽዳትና ውበት ዓለም ዓቀፍ ተወዳዳሪነት – አዲስ አበባ!

AMN- ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም

ከተማችን አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት፣ መልሶ ማልማትና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተሞሽራለች፥ ፍጹም ተቀይራለች፡፡ የከተማ ውበት ልክ መሆን ጀምራለች፡፡

መንገዶች ሰፍተወል፣ ጨለማ የነበሩ ጐዳናዎቿ በርተዋል፡፡ የእግረኛ መንገድ ተለይቶ ተገንብቷል፡፡ ከዚህ በፊት ያልነበሩ የብስክሌት መንገዶች የአዲስ አበባ መገለጫ መሆን ችለዋል።

ትላንት መንገዶች በመኪና ፓርኪንግ ይጨናነቁ ነበር ዛር ግን የለም፡፡ በየቦታው የመኪና ፓርኪንግ ቦታዎች ለምተዋል፡፡ የትራፊክ ፍሰቱንም እንዲሣለጥ የከተማዋ ውበት መጠበቅ ተችሏል፡፡

አዲስ አበባ 2.8 በመቶ ላይ የነበረውን አረንጓዴ ሽፋኗ ወደ 24 በመቶ አድጓል፡፡ ከአፍሪካ አስሩ ፅዱ ከተሞች አንዷ በመሆንም በዓለም አቀፍ ደረጃም እውቅናን አግኝታለች፡፡

አዲስ አበባ ጽዱ፡ ውብ እና መሰረተ ልማቶች የተሟሉላት ከተማ መሆን በመቻሏ በርካታ ኮንፈረንሶች፣ ስብሰባዎችና ጎብኚዎች የማስተናገድ ብቃቷ እያደገ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷ ይበልጥ ጎልብቶ፣ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን መላው አፍሪካውያን ዋና ከተማችን ብለው የሚጠሯት የጋራ ኩራታችን ሆናለች።

ከተማችን የነበራትን 74 በመቶ የጎስቋላነት ገጽታ ወደ 30 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል፡፡ በከተማችን ምንም እንኳን መሰረታዊ ለውጦች ቢመዘገቡም ዛሬም ብዙ መስራት ይጠበቃል፡፡

ለዚህም በቀጣይ በጀት ዓመት የሚተገበሩ የትኩረት ማዕከል ተብለው የተለዩ ዋናዋና ተግባራት በዋናነትም ከተማችን አዲስ አበባ ለነዋሪዎች ምቹ እና ዓለም አቀፍ ተወደዳሪ ከተማነትዋን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review