በመዲናዋ በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

You are currently viewing በመዲናዋ በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

AMN- ነሐሴ 18/2018 ዓ.ም

አደጋው የደረሰው ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 1:50 ሰዓት በቦሌ ክፍል ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡

የጉዞ አቅጣጫው ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ የሆነ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-05997 ትግ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መካከል 5 ወንዶችና 1 ሴት ህይወት አልፏል፡፡

ከሟቾች በተጨማሪ በታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ የሚገኙ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review