ምክክሩ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ከመሣሪያ አፈሙዝ ወደ ውይይትና ንግግር ያሸጋገረ ነው

You are currently viewing ምክክሩ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ከመሣሪያ አፈሙዝ ወደ ውይይትና ንግግር ያሸጋገረ ነው

AMN – ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ሂደት የዘመናትን የፖለቲካ ባህል ከኃይል ወደ ውይይትና ንግግር ያሸጋገረ፣ እንዲሁም ሀገር በቀል እውቀቶችን መሠረት ያደረገ ታሪካዊ መድረክ መሆኑን የሰላምና ጸጥታ መምህርና ተመራማሪው አቶ አሌክስ ብርሃኑ ገለጹ።

አቶ አሌክስ ብርሃኑ ከኤ ኤም ኤን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት ከዘለቀው አላስፈላጊ መወዛገብ ወጥቶ፣ ህዝቡ ልዩነቶቹን ወደ ጎን በመተው በራሱ ጉዳይ ላይ በጋራ መምከሩ ትልቅ የፖለቲካ ድል መሆኑን አንስተዋል።

ከዚህ ቀደም እንደ ኋላቀር ይታዩ የነበሩ ሀገር በቀል እውቀቶችና ተቋማት በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋል መጀመራቸው፣ ኢትዮጵያውያን የጋራ ችግሮቻቸውን በራሳቸው ለመፍታት የሚያስችል አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን ጠቁመዋል።

ምክክሩ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ እና ማዕከላዊ አካባቢዎች ያሉ ማኅበረሰቦችን ያካተተ በመሆኑ፣ ያልተወከለ የኅብረተሰብ ክፍልም ሆነ ሐሳብ የሌለ ሁሉን አቀፍና አሳታፊ ሂደት እንደነበር አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያውያን በፖለቲካ፣ በሃይማኖት እና በብሔር ልዩነቶች ቢኖራቸውም፤ በኢትዮጵያ ሰላም፣ ልማት እና አንድነት ላይ ግን ከጠባብ አመለካከት ወጥተው “ሀገር አሸናፊ በሆነችበት” የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸው የምክክሩ ትልቁ ውጤት መሆኑን ምሁሩ አመላክተዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review