የአፍሪካ የጤና ቱሪዝም መዳረሻ እና የልምድ ማዕከል- አዲስ አበባ

AMN- ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ተቋማትን በመገንባት የዜጎችን ሕይወት ለማሻሻል ያደረገችው ጥረት ውጤት እያመጣ መሆኑን ያስታወቁት ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች፣ አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ የጤና ቱሪዝም መዳረሻ የመሆን ራዕይዋን በተጨባጭ እያሳካች መሆኗን ገለጹ።

አዳዲስ የጤና ተቋማትን በፍጥነት በመገንባት፣ ተደራሽነትን በማስፋት እና የሰው ኃይልን በአስተማማኝ ሁኔታ በመገንባት ረገድ የተከናወኑ ሥራዎች የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የልማት ጉዞ የሚያሳዩ እንደሆኑ ተመላክቷል።

የአፍሪካ የጋራ ቤት እና የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው አዲስ አበባ፣ የሀገሪቱን የጤና ቱሪዝም መዳረሻ የመሆን ሀገር አቀፍ ውጥን እውን ለማድረግ ሰፊ ሥራዎችን አከናውነለች።

ከኤ ኤም ኤን ጋር ቆይታ ያደረጉት የአፍሪካ ኮንስቲቱዌንሲ ዳይሬክተር ሄነሪ ሆሞንዳ (ዶ/ር)፣ ከተማዋ ዘመናዊ አሰራርን በመዘርጋት እና መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት በጤናው ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እያመጣች መሆኑን ተናግረዋል።

የታደሱትና የተገነቡት ተቋማትም የመዲናዋን የጤና ቱሪዝም ርዕይ እውን የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።

ኬንያዊቷ ሜሪ ሞዳኒ በበኩላቸው፣ በከተሜነት ሂደት ውስጥ የተሳለጠ መሰረተ ልማት መገንባት፣ አገልግሎት ማሻሻል እና ከዚህም ጋር ጤናማ ትውልድን መገንባት እንደተጀመረ ገልጸዋል።

የኬንያ የጤና ዳይሬክተር ፓትሪክ አሞ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የመዲናዋ የሪፎርም ሥራዎች እና የጤና ቱሪዝም ሕልም በአፍሪካውያን ዘንድ እንደ ልምድ እና ተሞክሮ የሚቀመር መሆኑን አንስተዋል።

እነዚህን የጤና ዘርፍ ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ለማስፋፋት 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጉባኤ አሁንም በጉዳዩ ላይ መምከሩን ቀጥሏል።

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review