AMN – ነሐሴ 21/ 2018 ዓ.ም
በ2ተኛው የኢትዮጵያ ታዋቂ ፋይቲንግ ቻምፒዮንሺፕ (ETFC) “አድዋ ፋይት ናይት” በጉጉት የተጠበቀው የሴዶና ጆኒ ሚክስድ ማርሻል አርት ፍልሚያ በጆኒ አሸናፊነት ተጠናቋል።
የኢቲኤፍሲ 01 አሻናፊው ጆኒ ሴዶን በማሸነፍ ዳግም ክብሩን አስጠብቋል።
ጆኒ በመጀመሪያው ዙር ነው ተጋጣሚውን የረታው።
ይህ ውድድር በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ውስጥ በወጣቱ ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትን የፈጠረ ስፖርት ሆኗል።