AMN – ነሐሴ 22/ 2018 ዓ.ም
የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉአንግኬው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ጧት አዲስ አበባ ገብተዋል።
አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሲሃሳክ በቆይታቸው ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡
በውይይቱ የሁለቱን ሀገሮች የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እና የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ እንዲሁም የኢኮኖሚ ትብብርን ለማሳደግ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመለክታል።