የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል ምንጮችን በማስፋት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ገለፀ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል ምንጮችን በማስፋት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን ገለፀ

AMN – ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀሙን እና የ2019 እቅዱን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

ተቋሙ በመጪው በጀት ዓመትም የልማት ሥራዎቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ124 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ የቻለ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥም 39 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አረጋግጠዋል።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው አያይዘውም፣ ባለፉት ዓመታት አሰራርን በቴክኖሎጂ በመደገፍ፣ የኃይል ምንጮችን በማስፋት እና መሠረተ ልማቶችን በመላ አገሪቱ ማዳረስ ላይ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸው፤ በቀጣይም እነዚህ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በመግለጫው ይፋ እንደሆነው፤ በ2018 በጀት ዓመት በኃይል ሽያጭና የገቢ አሰባሰብ፣ በኃይል ማመንጨት የኦፕሬሽን ሥራ አፈፃፀም፣ እንዲሁም በማመንጫ፣ ማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ላይ አበረታች ውጤቶች ተመዝገበዋል።

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review