የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪፎርምን በመረጃ የመደገፍ ስራዎች እየተከናወኑ ነው – ትምህርት ሚኒስቴር

AMN- ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጥራትና አቅም ለማሳደግ መረጃን መሰረት ያደረገ ፣ ቀጣይነት እና ተጠያቂነት ያለው ስርዓትን ለመዘርጋት ያለመ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመታዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው ።

በቅርብ ጊዜ የተጀመረውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪፎርም በመረጃ የመደገፍ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸው የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ቱሽኔ ገለጹ።

ከውጭ የስልጠና ጥገኝነት ተላቀን የአመራሮችን አቅም ለመገንባት ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም አመራር ስራ ከመጀመሩ በፊት ወይም በስራ ላይ እያለ በእራሳችን አቀም ስልጠና እንዲያገኝ የሚያደርግ አሰራር መዘርጋቱንም ተናግረዋል ።

የድህረ-ምረቃ ተማሪዎችን ወጪ ጨምሮ ቀደም ሲል በግምት የሚሰሩ ስራዎችን ለማስቀረት በጥናት እና ምርምር ላይ የተመረኮዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

የተመራቂ ተማሪዎች የመቀጠር ምጣኔ እና በምን ያህል ጊዜ ስራ እንደሚይዙ የሚዳስስ ጥናት እየተካሄደ መሆኑንም ሚኒስትር ዴኤታው አንስተዋል።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት የሰውን ልጅ መተካት ባይችልም በትምህርት ተቋማት ውስጥ አጋዥ በመሆነ መንገድ ለመጠቀም ይሰራልም ብለዋል።

በዳንኤል መላኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review