ለአዲስ ዓመት በዓል አስፈላጊ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በበቂ ሁኔታ እየቀረቡ ነው

You are currently viewing ለአዲስ ዓመት በዓል አስፈላጊ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በበቂ ሁኔታ እየቀረቡ ነው

AMN- ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም

ለቀጣይ 2019 አዲስ ዓመት በዓል ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸውን አስፈላጊ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶችን በበቂ ሁኔታ ማቅረቡን የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ለአዲሱ ዓመት በዓል እስካሁን የተደረጉ የምርት አቅርቦት ዝግጅቶችንና ቀጣይ ስራዎችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ህብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽታዬ መሀመድ በሰጡት መግለጫ፤ ለበዓሉ ህብረተሰቡ የሚፈልጋቸው የፍጆታ ዕቃዎች በ11ቱም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ ህብረት ስራ ማህበራት በበቂ ሁኔታ መዳረሳቸውን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ከፌዴራል ህብረት ስራ ኮሚሽን እና ከክልሎች ጋር በመተባበር በገበያው ላይ ምንም ዓይነት የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን ኮሚሽነር ሽታዬ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት የጤፍ ምርት፣ ዱቄት እና ሌሎችም የኢንዱስትሪ ምርቶች እንዲሁም ዶሮ እና እንቁላል በህብረት ስራ ማህበራት እንዲሁም በኤግዚቢሽኖችና ባዛሮች መቅረባቸው ተመላክቷል።

በተጨማሪም የምግብ ዘይት በበቂ ደረጃ ለህብረተሰቡ መሰራጨቱ ኮሚሽነር ሽታዬ ገልጸዋል፡፡

ከስጋ አቅርቦት ጋር በተያያዘ 274 ስጋ ቤቶች ለህብረተሰቡ ለበዓል የሚሆን የእርድ በሬዎችን ለማቅረብ ዝግጅት ተጠናቋል ብለዋል።

በአለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review