አዲስ አበባ ያስመዘገበችው ታሪካዊ የልማት እመርታ

You are currently viewing አዲስ አበባ ያስመዘገበችው ታሪካዊ የልማት እመርታ

AMN- ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ በ2018 ዓ.ም በልማት እንቅስቃሴዎቿ አዲስ መልክ በመያዝ ለዘመናዊ ከተሜነት የሚመጥኑ ታሪካዊ ስኬቶችን አስመዝግባለች፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ሕዝብን ማዕከል ያደረጉ ስራዎችን በማከናወን የነዋሪዎችን ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ ከተማዋን ተወዳዳሪ አድርጓታል፡፡

በመዲናዋ ከተከናወኑ ዋና ዋና የልማት ስኬቶች መካከል የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት እንዲሁም የዲጂታል አገልግሎት ተጠቃሽ ናቸው።

የከተማዋን ገጽታ በቀየሩት የኮሪደር ልማት ስራዎች አማካኝነት የመንገዶች፣ የእግረኛ፣ የብስክሌት መንገዶች እና የመዝናኛ ስፍራዎች ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት መብቃት የከተማዋን ውበት ከፍ ከማድረግ ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ እንቅስቃሴን ፈጥሯል፡፡

በተጨማሪም በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተከናወነው የችግኝ ተከላ ሥራ የመዲናዋን የደንና አረንጓዴ ሽፋን አሳድጓል፡፡ ይህም ከተማዋን ንጹህ አየርና ጤናማ ስነ-ምህዳር እንዲኖራት አድርጓል።

በማህበራዊ አገልግሎትም የትምህርት፣ የጤና ተቋማት፣ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ እንዲሁም የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ተስፋፍተዋል።

ለአቅመ ደካሞች እና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎችም ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በዚህም አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡

እንዲሁም በአዲስ መሶብ የዲጂታል አንድ ማዕከል አገልግሎት በከተማ አስተዳደሩ የመንግስተ አገልገሎቶችን በቴክኖሎጂ የተደገፉ በማድረግ የቢሮክራሲ ማነቆዎችን በመቅረፍ ፈጣን አገልግሎት መስጠት ተችሏል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ጊዜያት የታዩትን እነዚህን አበረታች ስኬቶች በዘላቂነት ለማስቀጠል እና የተጀመሩትን የልማት ሥራዎች ከፍ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review