AMN-ጳጉሜን 1/2018 ዓ.ም
ማንችስተር ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ኤቨርተንን ገጥሞ 2ለ2 ተለያይቷል።
በሂልዲኪንሰን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የዩናይትድን ግቦች ብሪያን ምቡሞ እና ቤንያሚን ሼሽኮ አስቆጥረዋል።
ታሪቅ ጆርጅ እና ሚቲላንድ ናይልስ የኤቨርተንን ግቦች አስገኝተዋል።
የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች ሚቲላንድ ናይልስ 90+6ኛው ደቂቃ ላይ በማስቆጠር ነው ቡድኑ ነጥብ እንዲጋራ ያደረገው።
በሀል ሲቲ ተሸንፎ የጀመረው ዩናይትድ ከሦስት ጨዋታ አራት ነጥብ ይዟል። ምንም ጨዋታ ያልተሸነፈው ኤቨርተን አምስት ነጥብ አለው።
በሸዋንግዛው ግርማ