AMN መስከረም 2/ 2019
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከብሪክስ ጉባዔ ጎን ለጎን ከሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር የሁለቱን ሀገራት አጋርነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፤ የመከላከያ ትብብርን ማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታ፣ የማዕድን ዘርፍ እንዲሁም ወደ COP32 በሚደረገው ጉዞ ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሕንድ ጥልቅ ታሪካዊ ግንኙነት፣ የቆየ የባህል ትስስር እና በሕዝቦቻቸው መካከል ጠንካራ ወዳጅነት አላቸው ብለዋል፡፡
በመሆኑም የታሪክ እና የመልካም ፈቃድ ትስስሩን በቴክኖሎጂ፣ በክህሎት እና በኢንቨስትመንት አጋርነታቸውን ለማጠናከር አሁን ትክክለኛው ጊዜ መሆኑን ገልጸዋል፡፡